Menu Content/Inhalt

Other News

Cache Directory Unwriteable
EUPF PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 07 July 2004

  “ሁላችንም ከተረባረብን ወያኔ ከ3 ወር በላይ አይቆይም!” ትዋት ፖል ቻይ

 

twat EMF (5 march 2006) - ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት መከራ ውስጥ መውጣት የምትችለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሚያደርገው የህልውና ትግል እንጂ በውጭ ሃይሎች ጣልቃ-ገብነት ወይንም ጥገኝነት ያለመሆኑን አቶ ትዋት ፓል ቻይ የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር (ኢአአግ) መሬ አስታወቁ።

ትዋት ፓል ቻይ ይህንን ያስታወቁት በትላንትናው እለት ዘ ሄግ፡ ኔዘርላንድስ ላይ ተሰብስቦ ለንበረው በርካታ ኢትዮጵያዊ ባደረጉት ሰፊ ገለጻ ነው። በስብሰባው ላይ ከአውሮፓ የተውጣጡ የግንባሩ ድጋፍ ሰጪ ተወካዮች እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጭ ወራሪ ሃይሎች አልበገር ባይነቱን በአድዋ ድል ያስመሰከረ መሆኑን የገለጹት አቶ ትዋት ፓል ቻይ፡ ወራሪ ሃይሎች ኢትዮጵያን በቀጥታ መያዝ ስላቃታቸው በወያኔ ቅጥረኞች በመጠቀም ሕዝባችንን በዘር በመከፋፈልና ሀገሪቱን በመበታተን እየረገጡ በመግዛት ላይ መሆናቸውን ታሪክን በማጣቀስ አስረድተዋል። Read More...
Note: If you are unable to read the news, download Geez unicode here.


“የአድዋ ድል የተገኘው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ አመሉን በጉያ በመያዝ በራሱ ስንቅ፡ በራሱ መሬት እና በራሱ መሳሪያ በመረባረብ ነው። በአድዋ ድል የሚቆጩ ሃይሎች ወያኔን በቅጥረኝነት ላኩብን። የወያኔ ቡድን ኢትዮጵያን መሬትዋንና ስልጣንን እነጂ ሕዘቡን አይፈልገውም።” ይላሉ አቶ ትዋት ፓል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፋፍሎ የመግዛት ተልእኮ ለማስፈጸም የወያኔ ስርዓት ከ106 በላይ የዘር ፓርቲዎችን ማቛቛሙን አቶ ትዋት ገልጸው በያንዳንዱ ብሔር/ብሔረሰብ ከ 3 – 5 የሚሆኑ በወያኔ የተቀረጹ ፓርቲዎች ተፈጥረዋል፡ በጋመቤላ እንኳን 7 የብሔር ፓርቲዎች ሲፈጠሩ በትግራይ ግን አንድ ህወሃት ብቻ ነው ያለው ብለዋል።

ዜጎች ዋነኛ ጠላት የሆነውን ስርዓት ትተው፡ ህወሀት በቀደደው በር በመግባት እርስ-በርስ በመጠላለፍ የመለስ ዜናዊን ስርዓት ላለፉት 15 አመታት ማቆየታቸውን አቶ ትዋት በመቆጨት ይገልጻሉ።

ዛሬ የወያኔ ጠላት 70 ሚሊዮን ያትዮጵያ ሕዝብ ነው። ሀገሪቱ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃለች፡ በጣት የሚቆጠሩ የስርዐቱ አራማጆች በሕዝቡ ድህነት እነሱ ቢሊዮነሮች እየሆኑ የሀገሪቱን ገንዘብ 400 % ግሽበት ላይ እንዲወድቅ አድርገውታል። ….


ዳግማዊ አድዋ ጥሪ

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ የኢአአግን የሃገር እና የወገን ህልውና ጥሪ በመቀበል የህይወትና የደም መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ይገኛሉ። እንደ አቶ ትዋት አገላለጽ በአንድ ጊዜ ጥሪ ብቻ 4,170 ሰራዊት ወደ ግንበሩ ተሰማርቷል። ለዚህ የመኖር እና ያለመኖር ጥሪ ከሁዋላ ደጀን በመሆን በገንዘብ እና በማቴሪያል ድጋፍ እንዲሰጡ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲረባረቡ አቶ ትዋት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ሁሉም በየዘርፉ ከተረባረበ ኢትዮጵያ ነጻ ልትወጣ 3 ወር በላይ የማይፈጀባት ሁኔታ መፈጠሩን በመናገር አቶ ትዋት የበሰለና የሰከነ ገለጻቸውን ደምድመዋል። “ሁላችንም ከተረባረብን ወያኔ ከ 3 ወር በላይ አይቆይም!”

አቶ ትዋት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች በመዘዋወር ለ ኢትዮጵያውያን ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ይህ ጉበኝታቸው ግን የመጨረሻ መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ እንደነበር ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። ሀገሪቱን ካለችበት አዘቅት ለማውጣትና ዜጎችን ከወያኔ ሰቆቃ ለማዳን በ አውሮፓ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የገንዘብ መዋጮ በማድረግ ለግንባሩ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ችለናል።

Note: If you are unable to read the news, download Geez unicode here.

Last Updated ( Monday, 29 May 2006 )
 
< Prev   Next >