Menu Content/Inhalt

Other News

Cache Directory Unwriteable
+u c.} c- u H ) PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Friday, 02 June 2006
ድል በአንድነት ማሕበር (ድአማ) በስዊድን

Unity for the Best of Ethiopia

አራት ግንባሮች ግንባር ለግንባር ተገናኝተው በመወያየት አንድነትን ፈጥረዋል።

የድልና የብልጽግና ሁሉ መሰረቱ አንድነት ነው። ”ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ ያለ አንድነት ዕድገት፤ ብልፅግና፤ የሀገር ክብርና፤ የወገን በጎነት ሊኖር አይችልም። ሀገራችንን ከተተበተበችበት ችግር ለማውጣት የሚያስችለው ብቸኛው መንገድ ለአንድነትና ለነፃነት በአንድነት መታገል ነው። በአገራችን ከሰላሳ ዓመት በላይ የተደረጉት ትግሎችና የተከተልናቸው የትግል ስልቶች ያስከተሉት የሃገር ውድቀትንና የሕዝብ ውርደትን ብቻ በመሆኑ ከንግዲህ የምናካሂደው ትግል ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል።
ድልና ውጤት ያላስመዘገበ ለውድቀት የዳረገንን ስልት ይዞ መጓዝ የአገራችንና የራሳችን መቃብር ለመቆፈር የምናደርገው የጅል ጨዋታ እንጅ የኢትዮጲያዊ ጀግንነትና የብስለት መመዘኛ ስለማይሆን ቆም ብለን እንድናስብ ግድ ይላል። የመኖር ህልውናችን እንዲቀጥል፣ ኢትዮጲያ በኢትዮጲያነቷ እንድትኖር ሳያደናግር የሚያሰባስበንንና ነፃነት የሚያጎናፅፈንና ስልት ተመካክረን በጥንቃቄ ከመምረጥ ሌላ አማራጭ የለም። ድል በአንድነት የኢትዮጵያን፡ አንድነት፡ መሰረት፡ በማድረግ፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ነፃነት፡ በአማራጭ፡ ትግሉ፡ ከወያኔ፡ ጋር፡ በተናጠል፡ የሚታገሉ፡ ግንባሮችንና፡ ለወደፊትም፡ ለመታገል፡ የሚነሱ፡ ወገኖች፡ አንድነት፡ ፈጥረው፡ እንዲታገሉ፡ ለማድረግ ዝግጅት እንደሚያደርግ ከዓላማዎቹ አንዱ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል።

ስለሆነም ድል በዓንድነት በዓማራጭ ትግሉ በተናጠል ተሰማርተው በመታገል ላይ ያሉትን ግንባሮች በዓንድነት የሚታገሉበትን የአንድነት ግንባር ይፈጥሩ ዘንድ ድል በአንድነት መድረኩን በመፍጠር የተለያዩ ግንባሮች ከ ሜይ 26 እስከ ሜይ 27 ግንባር ለግንባር ተገናኝተው አንድነታቸውንና ልዩነታቸውን እንዲሁም መፍትሄውን እንዲወያዩ አድርጓል፡፡ ውይይቱን እንዲካፈሉ የሚታወቁ ግንባሮች በሙሉ ግብዣ የተደረገላቸው ሲሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግምባር እስከመጨረሻው እልት ድረስ አወንታዊ መልስ ካሳዩን በኋላ ስብሰባውን እንደማይካፈሉ ገልፀውልናል። ምክንያታቸውንም እንዲሰጡን በመጠባበቅ ላይ ነን።


በዚህ ውይይት
1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት አርበኞች ግንባር
2. የኢትዮጵያ ዲሞክራሳዊ አንድነት ግምባር
3. የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግምባር
4. ታጠቅ የኢትዮጲያ አንድነት ግምባር ተካፍለዋል።

በዚህ ዝግ ስብሰባ አንድነትና ልዩነት በሚለው አርዕስት ላይ ግምባሮቹ እስከዛሬ እንዳይቀራረቡና አብረው እንዳይሰሩ ምክንያትና መፍትሄ በሆኑ ነጥቦች ዙሪያ በዝርዝር ተወያይተው ያለፉትን ሥህተቶች በትምህርት ሠጭነታቸው ግንዛቤ በመውሰድ ሠፊና መሠረታዊ የሆኑ ውይይቶች በጥሩ መንፈስ ከተካሄዱ በኋላ በሁሉም ግምባሮች ሙሉ ፈቃድና ፅኑ ዕምነት በሥምምነት አንድነት ፈጥረዋል:: አሁን የተፈጠረው አንድነት ግንባር ሥም እንዲሠየምለት በቀረበው ሃሳብ ውይይት ተደርጎ የኢትዮጵያ አርበኞች ብሔራዊ አንድነት ኃይል (ኢአብአኃ) የአንድነት ግንባሩ መጠሪያ ሥም ሆኖ እንዲሠየም ሁሉም ግምባሮች ተቀብለው በሙሉ ድምፅ ተስማምተዋል::

ውህደቱ በሦሥት (3) ወር ጊዜ ውስጥ እንዲፈፀም ውህደቱን ተከታትሎ የሚያሥፈፅም አንድ ኮሚቴ ሠይሟል:: የአዲሱ ኮሚቴ ሥራም አራቱንም ግምባሮች ማሥተባበርና ውህደቱ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲከናወን ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ በተባበሩት ልጆቿ ትግል ነፃ ትወጣለች !

ድል በአንድነት

ስቶክሆልም/ስዊድን
28 May 2006

Last Updated ( Friday, 02 June 2006 )
 
< Prev   Next >